Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የሌዘር ዐውደ ርዕይ እና የዓለም የቆዳ ጉባዔ እንድታስተናግድ ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ 12ኛውን የመላው አፍሪካ የሌዘር አውደ ርዕይ እና 5ኛውን የዓለም የሌዘር ጉባኤ እንድታስናግድ መመረጧ ተገለፀ፡፡

ባለፉት አሥርት ዓመታት ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የሀገር ውስጥ ምርት እንዲያድግ የሚያበረታታ እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደነበርም በኢትዮጵያ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የቆዳና ጨርቃ ጨርቅ ዳይሬክተር አቶ ዘሪሁን አበበ ተናግረዋል፡፡

12 ኛውን የመላው አፍሪካ የቆዳ ዐውደ ርዕይ እንዲሁም 5 ኛውን የዓለም የቆዳ ጉባኤ ለማስተናገድ የተመረጠችውም በዚሁ ምክንያት እንደሆነ ነው የተገለፀው፡፡

የንግድ ትርኢቱ እና የጉባኤው መካሄድ ዓለም አቀፉን ገበያ ዘልቆ በመግባት ሀብቶቻችንን ለገበያ ለማቅረብ ትልቅ አስተዋፅዖ ይኖረዋልም ነው የተባለው፡፡

በጉባዔው ከ50 ሀገራት የተውጣጡ የዘርፉ አመራሮች እና ከ 5 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች እንደሚገኙ ነው የተገለፀው፡፡

ጉባኤው ከፈረንጆቹ ከሕዳር 3 እስከ 6 2021÷ ‹ቆዳ የተፈጥሮ ፀጋ› በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሲሆን÷ በተሳታፊዎች መካከል የእውቀት እና የቴክኖሎጂ ሽግግር እድሎች ይፈጠሩበታል መባሉን ከንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.