Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ህንድ የሃገራቱን ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶችን ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከህንዱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጃይሸንከር ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው ወቅት የሃገራቱን ግንኙነት ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማሳደግ በሚቻልበት አግባብ ላይ ውጤታማ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ወዳጅነታቸውን ወደ ባለብዙ ወገን ግንኙነት ማሳደግ በሚቻልበት አግባብ ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት ማጠናከር የሚያስችሉ የተለያዩ ስምምነቶች መፈራረማቸውንም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡

በዚህም የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ላላቸው ከቪዛ ነጻ እንዲገቡ ስምምነት ደርሰዋል፡፡

እንዲሁም ወሎ ዩኒቨርሲቲ እና የህንዱ የቆዳ ምርምር ኢንስቲቲዩት በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.