Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን የገቢ አሰባሰብ ላይ የልምድ ልውውጥ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ውጤታማ የገቢ አሰባሰብ ላይ የልምድ ልውውጥ ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ፒቲያ ሞርጋን የተመራ ልዑካን ቡድን በካሽ ሬጂስተር አተገባበር ከኢትዮጵያ ልምድ ለመቅሰም ከገቢዎች ሚኒስቴር የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴርን በመወከል የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የሚኒስትር የታክስ አማካሪ አቶ ነብዩ ሳሙኤል፤ ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ ልምድ በመውሰድ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ተግባራዊ ማድረጓን በመግለፅ ደቡብ ሱዳን ካሽ ሬጂስተርን ተግባራዊ ለማድረግ ከኢትዮጵያ የምትወስዳቸው ልምዶች እንዳሉ አብራርተዋል፡፡

ይበልጥ ተቀራርቦ በመስራት ኢትዮጵያ የካሽ ሬጂስተር ማሽን ተግባራዊ ስታደርግ ያጋጠማት ችግር እና የወሰደችው መፍትሄ ለደቡብ ሱዳን ልምድ እንደሚሆን እና ካሽ ሬጂስተርን በትክክል ተግባራዊ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ጀምስ ፒቲያ ሞርጋን በበኩላቸው፤ ከኢትዮጵያ ጋር በመልካም ጊዜ እና በፈታኝ ወቅት በጋራ እንደሰራን ሁሉ በገቢ አሰባሰብ ዙሪያ ሀገራቸው በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል፡፡

በገቢ አሰባሰብ በጋራ ለመስራት የሁለቱ አገራት ዜጎች የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ተቀራርቦ መስራት ይገባልም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የካሽ ሬጂስተር ማሽን አተገባበር በተመለከተ ለልዑካን ቡድኑ በባለሙያዎች ማብራሪያ መሰጠቱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.