Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የባህር-አየር ካርጎ አገልግሎት ለመጀመር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና የጂቡቲ የነፃ ቀጠናና ወደብ ባለስልጣን በጋራ በመሆን የባህር-አየር ካርጎን በመጀመር የሸቀጦችን ዝውውር በማቀላጠፍ የአህጉሪቱን ንግድ ይበልጥ ማሳለጥ በሚቻልበት ዙሪያ ለመስራት ተስማምተዋል።

በተለይ ከቻይና ወደ አፍሪካ የሚሻገረው ከ400 ሺህ ቶን በላይ ምርትና ሸቀጥን በባህር-አየር በማያያዝ ከጂቡቲ ወደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ፈጣን የካርጎ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።

ይህ ውጤታማ ከሆነ የአየር መንገዱን የካርጎ አገልግሎት በእጥፍ ሊያሳድግ እንደሚችል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት አስታውቋል።

በውይይቱ በጂቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ፣ የጂቡቲ ነፃ ቀጠናና ወደብ ባለስልጣን ሊቀመንበር አቡበከር ኡመር ሃዲ፣ የኢትዮጵያ እና የጂቡቲ አየር መንገድ ተወካዮች፣ የቻይና የንግድ ጉዳዮች ሃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.