Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ጃፓን የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ መስኮች በትብብር ይሰራሉ – ረ/ፕ በለጠ ሞላ

አዲስ አበባ፣ጥቅምት 16፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ በኢትዮጵያ ከጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ጋር ተወያዩ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ረዳት ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ÷ ኢትዮጵያና ጃፓን የቆየ ወዳጅነት ያላቸው ሃገራት መሆኑን ገልጸዋል።
አያይዘውም ኢትዮጵያ ከጃፓን በአስቸጋሪ ወቅት እና ሌሎች ጊዜዎች አስፈላጊ ድጋፍ እንደተደረገላትም አንስተዋል።
በቀጣይም እንደ ሀገርና እንደ ተቋም በጋራ ጉዳዮች በተለይም በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን መሰረተ ልማት፣ በኤሌክትሮኒክና የኢንቨስትመንት ስራን በማሳለጥ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያረጋግጡ መስኮች በትብብር እንሰራለን ብለዋል።
የጃፓን አምባሳደር ኢቶ ታካኮ በበኩላቸው÷ ጃፓንና ኢትዮጵያ በጋራ በሚሰሩባቸው የቴክኖሎጂ ጉዳዮች፣ በተቋሙና በጃፓን መሰል አቻ ተቋማት ስለሚኖረው ትብብር እና የወደፊት አጋርነት ላይ ለመወያየት መምጣታቸውን ጠቁመዋል።
ጃፓን በመሠረተ ልማት ግንባታ፣ በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ፣ በሰው ሐብት ልማት ድጋፍ ስታደርግ እንደነበር ጠቅሰው፥ ወደ ፊትም ለኢትዮጵያ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ የቴሌኮም ዘርፍ እንድትሳተፍ ያገኘችውን እድል በማንሳትም ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ሌሎች ተቋማት ጋር በትብብር መስራታቸውን እንደሚቀጥሉ ማረጋገጣቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.