Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላቸውን የዘመናት ትብብር አጠናክረው ይቀጥላሉ-ወ/ሮ ዳግማዊት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ በኢትዮጵያ ከጅቡቲ አምባሳደር አብዲ መሃሙድ ኢያቤን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ወይዘሮ ዳግማዊት ኢትዮጵያና ጅቡቲ በተለያዩ ዘርፎች ለዘመናት የቆየ ጥብቅ ግንኙት ያላቸው እህትማማች አገራት መሆናቸውን አውስተዋል፡፡
የአገራቱ ግንኙነት በዘርፈ ብዙ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ጠንካራ መሆኑን ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት፡፡
በተለይም አገራቱ በአቪዬሽን መስክ የገነቡት ጥብቅ ገንኙነት ለቀጠናው ጭምር ትልቅ አቅም መሆኑን የጠቆሙት ወ/ሮ ዳግማዊት÷ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
አምባሳደር አብዲ መሃሙድ ኢያቤ በበኩላቸው÷ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስክ ያላቸው የሁለትዮች ትብብር የላቀ እንደሆነ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በውይይቱ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው መንግስቴ ኢትዮጵያና ጅቡቲ በአቪዬሽን መስክ ስላላቸው ትብብር ገለፃ አድርገዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.