Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ተስማሙኢትዮጵያ እና ፈረንሳይ በንግድ እና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የፈረንሳዩ ሜዴፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ወደላቀ ደረጃ እንዲደርስ በቅንጅት ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ሜዴፍ የፈረንሳይ ድርጅቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢንቨስትመንት ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚሰራ እና የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን የሚደግፍ መንግስታዊ ያልሆነ ተቋም መሆኑ ተገልጿል፡፡

የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን በፈረንሳይ ፓሪስ በሚገኘው በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት ከሜዴፍ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፊሊፕ ጉቶር ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም ሁለቱ አመራሮች ተቋሟዊ ግንኙነትን ለማጠናከር በተለያዩ ዘርፎች አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነወ መረጃ ያመላክታል፡፡

በቅርቡም የሜዴፍ ልዑክ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ ዕቅድ መያዙ ነው የተገለጸው፡፡

ልዑኩም በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች በግብርና ማቀነባበሪያ፣ በአምራች ዘርፍ እና በሃይል ዘርፎች መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት ያሳዩ የፈረንሳይ ባለሀብቶችን ይዞ ለመምጣት ዕቅድ እንዳለው አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.