Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ድንበር አካባቢ የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የጀመረችውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለፀ

 አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ እና ሱዳን አዋሳኝ ድንበር የተፈጠረውን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመቅረፍ የተጀመረውን ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢፌዴሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቃባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታወቁ።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡትመግለጫ፣ በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ ተፈጥሮ የነበረው ችግር በአሁኑ ሰዓት ውጥረቱ ቢቀንስም፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ችግሩን ለመፍታት ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ከሱዳን እና ከኢትዮጵያ ግጭት ለማትረፍ የሚሠሩ ኃይሎች እጃቸውን ባስገቡበት በዚህ ግጭት የኢትዮጵያ መንግሥት እንደማይገባም ጠቅሰዋል።
አንዳንድ የሱዳን መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በጉዳዩ ላይ አልተሳተፉም ማለት አይቻልም ብለዋል ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው።
አካባቢው እንዲተራመስ የሚፈልጉ አካላት እንዳሉ የተናገሩት ቃል አቀባዩ እነዚህ ሰዎች በሱዳን በኩል የጀመሩት ችግር ቢከሽፍባቸው በሌላ ቦታ ሊጀምሩ ይችላሉም ብለዋል።
በመግለጫቸው በትግራይ ክልል ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ይዘውት የነበረው አቋም ወደ ትክክለኛ መንገድ እየመጣ መሆኑንም ቃል አቀባዩ አስረድተዋል፡፡
ተቋማቱ ከዚህ ቀደም የነበራቸውን አቀቋም ቀይረዋል ያሉት አምባሳደር ዲና ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ጋር በተያያዘም ዜጎችን ወደ ሃገራቸው መመለስ መቻሉን አውስተዋል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞም ከሳዑዲ ዓረቢያ 286 እንዲሁም ከሊባኖስ 42 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋልም ነው ያሉት፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.