Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ የ210 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አገኘች

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች የከርሰ ምድር ውሃን ለማልማትና ጥቅም ላይ ለማዋል የሚያስችል የ210 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ አገኘች፡፡

ድጋፉ የዝናብ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች የከርሰ ምድር ውሃን በማልማት ለመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን እንዲሁም ለመስኖ ልማት ለማዋል ለተቀረጹ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የሚውል ነው ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቶቹ በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርና በመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ሚኒስቴር በ5 ዓመታት ውስጥ የሚተገበሩ ሲሆን÷በቆላማ አካባቢ የሚኖሩ የሀገሪቱን ወገኖች ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮችና ባለሙያዎች ከዓለም ባንክ ልዑክ ጋር የተወያዩ ሲሆን÷ የድጋፍ ስምምነቱ በገንዘብ ሚኒስቴር ከተፈረመና በሀገሪቱ ፓርላማ ከፀደቀ በኋላ ተግባራዊ ይሆናል ነው የተባለው፡፡

ፕሮጀክቶቹ በምሥራቅ አፍሪካ ሀገሮች ውስጥ የከርሰ ምድር ውሃ በብዛት በሚገኝባቸው፣ ዝናብ አጠርና ቆላማ በሆኑ አካባቢዎች በዓለም ባንክ ድጋፍ የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች አካል መሆናቸውን ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.