Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከዓመታዊ በጀቷ 11 በመቶ ለመንገድ መሠረተ ልማትና ጥገና መድባለች – ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ዛሬ በቤጂንግ በተጀመረው 2ኛው የተመድ ዓለም አቀፍ ዘላቂ የትራንስፖርት ኮንፈረንስ መክፈቻ ላይ ንግግር አድርገዋል።

በዚህ ወቅት የመንገድ መሠረተ ልማት በግብርና ላይ ለተመሰረተው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት እና ዋነኛ የልማት አጀንዳ በመሆኑ ከዓመታዊ በጀቷ 11 በመቶ ለመንገድ መሠረተ ልማት እና ጥገና መድባለች ብለዋል።

ኮንፍረንሱ እንደ እኛ ወደብ አልባ ለሆኑ ሀገራት ትኩረት አንደሚሰጥ ተስፋቸውን መግለጻቸውን ከፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ፕሬዚደንቷ በአነስተኛ የገጠር ከተሞችም ሆነ በአዲስ አበባ የሰዎችንም ሆነ የቁሳቁስ ዝውውርን ለማፋጠን በቀላል የኤሌክትሪክ ባቡርም ሆነ ፈጣን የመጓጓዣ ሥርዓት በመፍጠር ጉዞን አስተማማኝ ማድረግ ለዘላቂ ልማት መምጣት ወሳኝ መሆናቸውን አስምረውበታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.