Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ወደ ትርምስ ትገባለች የሚለው ስጋት የሃገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ካለመረዳት የመነጨ ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተለያዩ ወገኖች ኢትዮጵያ ወደ ትርምስ ትገባለች የሚለው ስጋታቸው የማይሆን እና የሃገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ካለመረዳት የሚመነጭ መሆኑን ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የኢትዮጵያ ወዳጆች በሃገሪቱ ስላለው ሁኔታ ለሰጡት ትኩረት መንግስት ደስተኛ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ ወደ ትርምስ ትገባለች የሚለው ስጋታቸው የማይሆን እና የሃገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ ካለመረዳት የመነጨ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

አሁን እየተካሄደ ያለው ህግ የማስከበር ስራ ሰላምንና መረጋጋትን በማስፈን ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ ያለመ ነው ብለዋል፡፡

ህግ የማስከበሩ ተልዕኮ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅም በመልዕክታቸው ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.