Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ውስጣዊ ችግሯን በራሷ የመፍታት አቅም አላት – በኢትዮጵያ የባንግላዴሽ አምባሳደር

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 16 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በኢትዮጵያ ከባንግላዴሽ አምባሳደር ማዝሩል ኢስላም ጋር ውይይት አካሂደዋል ።

በውይይታቸውም አምባሳደር ማዝሩል እንደገለፁት ኢትዮጵያና ባንግላዴሽ የቆየ ግንኙነትና ወዳጅነት አላቸው።

አያይዘውም አገራቱ በተለይ በስፖርትና በባህል ዘርፍ ሰፊ ሀብት ያላቸው በመሆኑ በቀጣይ በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ከወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ አገራቸው ኢትዮጵያ የገጠማትን ወቅታዊ ችግር እንደምትገነዘብና፥ ችግሮቿን ያለማንም ጣልቃ ገብነት በውስጥ አቅሟ መፍታት እንደምትችል ገልፀዋል።

በዚህ ወቅትም ባንግላዴሽ ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም መግለጻቸውን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚያሰራጩት የተጋነነ እና ከእውነት የራቀ ዘገባ አሁናዊ የአገሪቱን ሁኔታ ያላገናዘበ እንደሆነና አዲስ አበባ በጥሩ መረጋጋት ያለ እንደምትገኝ አስረድተዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት በበኩላቸው የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ለአምባሳደሩ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን፥ ባንግላዴሽ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ አቋም በመያዝ ኢትዮጵያ የውስጥ ችግሯን በራሷ እንደምትፈታ ለምታደርገው ጥረት ያላቸውን አድናቆት ገልፀዋል ።

አያይዘውም የሁለቱን አገራት ግንኙነት በማጠናከር በባህልና ስፖርት ዘርፍ በጋራ ለመስራትና ልምድ ለመለዋወጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተደጋግፈው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ጠቅሰዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.