Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በመጠቀም ሱዳን እና ግብፅን የመጉዳት ዓላማ የላትም- ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያ በግንባታ ላይ የሚገኘውን ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብን በመጠቀም ሱዳን እና ግብፅን የመጉዳት ዓላማ እንደሌላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ75ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ አጠቃላይ ክርክር ላይ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተሳትፈዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ለ193 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ባደረጉት ንግግር በደንብ ግልፅ ላደረግ የምፈልገው እኛ እነዚህን ሀገራት የመጎዳት ፍላጎት የለንም ብለዋል።
በአፍሪካ ህብረት መሪት እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት ላይ ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ለሚያነሷቸው አሳሳቢ ጉዳዬች ትኩረት እንደምትሰጥ በመግለፅ የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ለመድረስ ጠንካራ ተነሻስነት እንዳለት ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዳሴ ግድብ በታችኛው የተፋሰስ ሀገራት በትነት ሊባክን የሚችለውን ውሃ ለመጠበቅ እንደሚያስችልም አንስተዋል።
በመሰረታዊነት ከንፁህ የሀይል ምንጭ የኤሌክትሪክ ሀይል ፍላጎታችንን ለማሳካት እየሰራን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ 65 ሚሊየን ህዝባችንን በጨለማ ውስጥ አስቀምጠን መቀጠል አንችልም ብለዋል።
የበርሃ አንበጣ ወረርሽኝ፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በሚሊየን የሚቆጠር ህዝባችን ላይ የተለያዩ ቀውሶች ሊያስከትል ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን ለውጥ ለማስቀጠል ያላቸውን ተነሳሽነት እና ፍላጎት ለተሳታፊዎቹ ገልፀዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.