Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የሴካፋ ውድድር ሻምፒዮን ሆነች

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 30 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዙሩ ካደረጋቸው 4 ጨዋታዎች ሁሉንም በአሸናፊነት በማጠናቀቅ ሻምፒዮን ሆነ ።

ብሄራዊ ቡድኑ 12 ነጥብ በመያዝ 12 ነጥብ ካለው ዩጋንዳ አቻው ጋር የመጨረሻውን የዋንጫ ጨዋታ በዛሬው ዕለት ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት ባደረገው ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን የሆነው ።

በዩጋንዳ አስተናጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የምስራቅና መካከለኛ አፍሪካ ሀገራት ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድኖች ውድድር በስድስት ሀገራት መካከል በዙር ሲካሄድ ቆይቶ ዛሬ በተደረጉ ሦስት የመጨረሻ ጨዋታዎች ተጠናቋል።

በውድድሩ ኢትዮጵያ ሻምፒዮን በመሆን የዋንጫ እና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ስትሆን ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ በቅደም ተከተሉ መሠረት የብርና የንሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.