Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሩስያ ስብሰባ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ያላትን ፍላጎት ገለፀች

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2022 የሚካሄደውን ሁለተኛውን የአፍሪካ ሩስያ ስብሰባ በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ያላትን ፍላጎት ገልፃለች።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአምባሳደር ደረጃ ከአፍሪካ ሩስያ የትብብር ፎረም ፀሃፊ ኦሌግ ኦዜሮቭ ጋር ተወያይተዋል።

በዚህ ወቅትበ2022 በአፍሪካ የሚካሄደውን የአፍሪካ ሩስያ ስብሰባ ዝግጅት አስመልክቶ ውይይት አድርገዋል።

አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ ከሩሲያ ጋር ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላትን ፍላጎት ለፀሃፊው ገልፀዋል።

ሩስያ ይህን መድረክ ለመፍጠር የወሰደችውን ተነሳሽነት ያደነቁት አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የአፍሪካ ሩስያ ጉባኤ በአዲስ አበባ ለማዘጋጀት ያላትን ፍላጎት ገለፀዋል።

ኦሌግ ኦዜሮቭ በበኩላቸው ስለ ፅህፈት ቤታቸው ስራ እና ሃላፊነት ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የአፍሪካ እና ሩስያ ኩባንያዎችን በጋራ እንዲሰሩ የሚያስችል የኢኮኖሚ ትብብር ማህበር እንደተቋቋመም ለአቶ ደመቀ ገለፃ አድርገዋል።

የስብሰባው ዝግጅት አካል የሆነ ውይይት በመጪው ክረምት ከአፍሪካ ህብረት ከአፍሪካ ሀገራት ጋር እንደሚከናወንም ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ በደህንነት ፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራ ፣ ግብርና ፣ ሀይል ፣በኒውክሌር ጤና እና በስነ ምድር ምርምር(geology exploration) ያላቸውን ትብብር በተመለከተ ተወያይተዋል።

ፀሃፊው ኦሌግ ኦዜሮቭ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በሞስኮ ጉብኝት እንዲያደርጉ ግብዣ አቅርበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.