Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅት ተተኪ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጀኔቫ ሲዊዘርላንድ እየተካሄደ ባለው 75ኛው የአለም ጤና ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የአለም ጤና ድርጅት ተተኪ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል በመሆን ተመርጣለች።

ከአፍሪካ ኢትዮጵያና ሴኔጋል ናቸው ተተኪ የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል በመሆን የተመረጡት፡፡

በዚህም የተመረጡ አገራት በተወካዮቻቸው አማካይነት በዋናነት የአለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔን ውሳኔ ፣ አጀንዳ መቅረጽ፣ ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን ማስፈጸም እንዲሁም አስፈላጊ ምክረ-ሀሳብ በማቅረብ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በመከታተል የሚያስፈጽሙ ይሆናል መባሉን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.