Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የገጠማትን ችግር በራሷ አቅም ተወጥታ የከፍታ ጉዞዋን ጀምራለች- የሩሲያ አምባሳደር

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የገጠማትን የውስጥ ችግር በራሷ አቅም ተወጥታ የከፍታ ጉዞዋን ጀምራለች ሲሉ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጀኒ ተረኺን ገለፁ፡፡

በቅርቡ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ በተመለከተ አንዳንድ አገራት አለም አቀፍ ድርጅቶችን ተገን አድርገው ድብቅ ፖለቲካዊ አጀንዳቸውን በኢትዮጵያ ላይ ለመጫን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ሩስያ አጥብቃ እንደምትቃወም አመልክተዋል፡፡

በሁለቱ ሃገራት መካከል የተፈፀሙ ስምምነቶችን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸወን የጠቆሙት አምባሳደሩ፥ በቀጣይም አገራቸው በኢትዮጵያ ቀጣይ ጉዞ ወሳኝ የሆኑ ድጋፎችን አጠናክራ እንደምትቀጥል ቃል ገብተዋል፡፡

የሩስያ ገዢ ፓርቲ 20ኛ የምስረታ በአሉን በፑሽኪን የሳይንስና የባህል ማዕከል ያከበረ ሲሆን፥ በስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አደም የእንኳን ደስ ያላችሁ መልክት አስተላልፈዋል፡፡

በስነ ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያን እና የሩሲያን የረጅም ዘመን ግንኙነት እና የሁለቱ አገራት ገዢ ፓርቲዎች ትብብር የሚያሳይ የፎቶ ግራፍ አውደ ርዕይ የተዘጋጀ ሲሆን፥ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል እየተጠናከረ የመጣው የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት የሁለቱን አገራት የቆየ ወዳጅነት ለማጠናከር የጎላ ሚና እንደሚኖረው አምባሳደር ኢቭጀኒ ተረኺን ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በወንደሰን አረጋኸኝ

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.