Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ዩኔስኮና የዓለም ጤና ድርጅት በአማራ እና አፋር ክልሎች ህወሓት ያደረሳቸውን ውድመቶች በተመለከተ እውነቱን እንዲያወጡ ጠየቀች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) እና የዓለም ጤና ድርጅት በአማራ እና አፋር ክልሎች ህወሓት ያደረሳቸውን ውድመቶች በተመለከተ እውነቱን እንዲያጋልጡ ጠየቀች።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ዋና ዳይሬክተር ዮሴፍ ካሳዬ፥ ከዩኔስኮ እና ከዓለም ጤና ድርጅት የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅትም ህወሓት ትግራይን ጨምሮ በአማራ እና አፋር ክልሎች በአገሪቱ ባህላዊ ቅርሶች እና የጤና መሰረተ ልማቶች ላይ ያደረሰውን ውድመትና ጉዳት ከማውገዝ አንጻር ካሳዩት ቸልተኝነት ጋር በተያያዘ በመንግስት በኩል ያለውን አቋም አብራርተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ንብረቶችን ጨምሮ በመሰረተ ልማት ላይ የደረሰው ውድመት እና የንብረት ዘረፋ ከፍተኛ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን ነው በዚሁ ወቅት ያስረዱት።

አያይዘውም ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አሸባሪ ቡድኑ የፈጸመውን ድርጊት ለማውገዝ ያሳየው ቸልተኝነት ቡድኑ ተጨማሪ ጥፋት እንዲያደርስ የሚያበረታታ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ተመድ መስራች አባልነቷ ከሁሉም የተመድ ድርጅቶች ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንዳላትም አንስተዋል።

ከዚህ አንጻርም ድርጅቶቹ ሃላፊነታቸውን ነጻ ሆነው እንዲወጡና በአሸባሪው ህወሓት የደረሱ ውድመቶችን በይፋ ይናገራሉ ብላ ትጠብቃለች ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የድርጅቶቹ የስራ ሃላፊዎች በበኩላቸው የኢትዮጵያን ባህላዊ የመስህብ ስፍራዎች እና ኢትዮጵያውያንን ከመጠበቅ አንጻር የነበራቸውን ሃላፊነት ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የኢትዮጵያን ጉዳይ በአንክሮ ለመመልከት ቃል ገብተዋል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.