Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 17ኛውን የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም ታስተናግዳለች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በ2015 የሚካሄደውን 17ኛውን የኢንተርኔት አስተዳደር ፎረም እንደምታስተናግድ ተገለፀ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁርያ አሊ ከተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ ሉ ዤንሜን ጋር በፎረሙ ዝግጅት ዙሪያ በፖላንድ ተወያይተዋል።

ሉ ዤንሜን በአፍሪካ የበይነ መረብ ግንኙነት ዝቅተኛ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ የምታስተናግደው ቀጣዩ ፎረም ይህንን ችግር ለመቅረፍ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚጠቆሙበት ይሆናል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ገልፀዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ በበኩላቸው÷ አፍሪካን ከዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለማድረግና ከመሰረተ ልማት ጋር የተያያዙ ችግሮቿን ለመፍታት የምታደርገው ጥረት በዚህ መልኩ ከተደገፈ መልካም ውጤት እንደሚመዘገብ እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

16ኛው የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ በፖላንድ እየተዳሄደ ሲሆን÷ መድረኩ የተለያዩ ግለሰቦችና ባለድርሻ አካላትን በአንድ መድረክ በማምጣት ከኢንተርኔት ጋር የተያያዙ ፖሊሲዎች ላይ ውይይት የሚካሄድበት መሆኑን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዓለም 3 ቢሊየን የሚሆነው ህዝብ ምንም አይነት የቴሌኮምና የኢንተርኔት አገልግሎት እንደማያገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.