Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ 400 ሺህ የሚጠጋ የኮቪድ-19 ክትባት በቅርቡ እንደምታገኝ የጤና ሚኒስቴር ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ወደ 400 ሺህ የሚጠጋ የኮቪድ-19 ክትባት በቅርቡ እንደምታገኝ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ።

የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በኢትዮጵያ እየተሰጠ ባለው የኮቪድ-19 ክትባት እና በቀጣይ በሚሰጠው ሁለተኛው ዙር የክትባት መርሃ-ግብር ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ቫይረሱን የመከላከል አቅም ከመተግበርና ከማስተግበር ጎን ለጎን ክትባቱን ለማግኘት እየተደረገ ያለውን ጥረት ዘርዝረዋል።

በዚህም መንግስት ለኮቪድ-19 ክትባት ግዢ ተጨማሪ ፋይናንስ በመመደብ ክትባቱን በአይነትም ሆነ በመጠን ለመጨመር ከአለም አቀፍ ድርጅቶችና ከአፍሪካ ሕብረት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አያይዘውም የክትባቱን ተደራሽነት ለማስፋት ከሌሎች ድረጅቶች ጋር እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህም መሰረት 400ሺህ የሚጠጋ የኮቪድ-19 ተጨማሪ ክትባት በቅርቡ ከኮቫክስ አለም አቀፍ ጥምረት መምጣት እንደሚጀምር ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.