Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ  በሚል መሪ  ቃል በወላይታ ሶዶ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ኢትዮ-ሰላም ሩጫ በወላይታ በሚል መሪ  ቃል በወላይታ ሶዶ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄዷል፡፡

ሩጫው የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና ታላላቅ አትሌቶች በተገኙበት ተካሂዷል ።

የጎዳና ላይ ሩጫው 5 ኪሎ ሜትር መንገድ የሸፈነ ሲሆን፥ ገቢውም የቀድሞውን ዳሞታ አትሌቲክስ ቡድንን መልሶ ለማቋቋም ይውላል ተብሏል።

በሩጫው የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስትር  ዴኤታ አቶ ታዬ  ደንደአን ጨምሮ ሌሎች የክልልና  የዞን ከፍተኛ የሥራ  ኃላፊዎች  ተገኝተዋል፡፡

የኢፌዴሪ ሰላም  ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታዬ ደንዳኣ ስፖርት  መሥራትን ባህል በማድረግ  ከተለያዩ  የሰላም የጎዳና ላይ ሩጫዎች ልምድ ማድረግ  እንደሚገባ አሳስበዋል ።

የወላይታ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አድማሱ አወቀ በአትሌቲክስ ስፖርት ዘርፍ የተሳተፉትን ሁሉንም ያመሰገኑ ሲሆን፥ ይህንን ዕድል ወደ  ልማት ለማዞር  እንደሚሰራ ገልጸዋል ።

በተመሳሳይ የስፖርቱን ዘርፍ ለማነቃቃትና ተተኪ ሯጮችን ለማፍራት  ያለመው የጎዳና ላይ ሩጫ በዲላ ከተማ ተካሂዷል፡፡

በርካታ የስፖርት አፍቃሪዎች የተሳተፉበት የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫ ላይ ለቀጣይ ትውልድ ተተኪ ሯጮች የሚመለመሉ ሲሆን፥ በውድድሩ ከ1 እሰከ 3 ለወጡት ተወዳዳሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተብርክቶላቸዋል፡፡

በ”ውብ ሀገሬ ታላቁ የጎዳና ላይ ሩጫ” የዞኑ ዋና አስተዳደሪን  ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የስፖርት ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች  በተገኙበት ነው የተካሄደው።

 

በኢብራሂም ባዲና  ማታዎስ ፈለቀ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.