Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በብሮድባንድ ኢንተርኔት አግልግሎቱ ላይ የዋጋ ቅናሽ አደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በብሮድባንድ ኢንተርኔት አግልግሎቱ ላይ ማሻሻያ እና የዋጋ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።

በዚህም ለግል ተጠቃሚዎች እስከ 69 በመቶ፣ ለVPN አግልግሎት እስከ 72 በመቶ እንዲሁም ለኢንተርፕራይዞች እስከ 65 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ ማድረጉን ነው ያስታወቀው።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ፥ የአገልግሎት ማሻሻያው ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለፋይናንስ ተቋማት እንዲሁም ለሌሎችም የንግድ ተቋማት አገልግሎት ጥራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

በተለይም በመንግስት አገልግሎት ተደራሽነት እና ግልጽነት ረገድ የበኩሉን እንደሚወጣም ተጠቁሟል።

126 አመታትን ያስቆጠረው ኢትዮ ቴሌኮም በቅርቡ የ3 አመታት ስትራቴጂክ እቅድ ማውጣቱ ይታወሳል።

ማሻሻያው የደንበኞቹን ፍላጎት ለማርካት እና ለዓመታት በደንበኞቹ ይነሱ የነበሩ ጥያቄዎችን ምላሽ ለመስጠት ታስቦ የተደረገ ነው ተብሏል።

በምስክር ስናፍቅ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.