Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በእንጦጦ ፓርክ ስማርት ማማ አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ዘመናዊ በሆነ መንገድ የገነባቸውንና ጎብኚዎች በእንጦጦ ፓርክ የኢንተርኔት ዳታ አገልግሎት ማግኘት የሚያስችላቸውን የስማርት ማማ አስመረቀ፡፡

ማማው የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው በዛሬው ዕለት የተመረቀው፡፡

ስማርት ማማው የጎብኚዎችን ፍሰት መሰረት በማድረግ የፓርኩን ተፈጥሯዊ ገጽታውን በጠበቀ እና ለዕይታ ማራኪ በሆነ ዲዛይን የተተከለ ሲሆን በቀጣይም በፓርኩ ውስጥ ለሚከናወነው የ5ኛው ትውልድ ኔትወርክ ዝርጋታ ዝግጁ እንዲሆን መደረጉ ተጠቅሷል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ በቀጣይ ኢኮ ቱሪዝም በሚካሄድባቸው የተለዩ ስፍራዎች ጋር የሚመሳሰሉ የካሞፍላጅ ማማዎች እንደሚተከሉ ተጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም በእንጦጦ ፓርክ እንደ ማሳያ ተደርጎ የቀረበው ይህ ዘመኑ ያፈራው ቴክኖሎጂ በቀጣይም ስማርት ማማዎችን ከተለያዩ የመንግስት እና የግል ተቋማት ጋር በመተባበር የሚተክል መሆኑን ከኢትዮ ቴሌኮም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.