Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በ16 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የገዛቸውን ደብተሮች የመግዛት አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች ማሰራጨት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም ለ2014 የትምህርት ዘመን ከ16 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የገዛቸውን ከ600 ሺህ በላይ ደብተሮች በመላ ሀገሪቱ እያሰራጨ መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ÷ ተማሪዎችን ማገዝ የነገውን ትውልድ መገንባት ነው ብለዋል።

በመርሃ ግብሩ 600 ሺህ ደብተሮች እንደሚከፋፈሉ የተገለጸ ሲሆን ከ660 በላይ ትምህርት ቤቶች ተለይተው ከ50 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የተመረጡ ተማሪዎች ይከፋፈላሉ ተብሏል።

በዛሬው ዕለትም በደብረብርሃን ከተማ ከ1 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎች የደብተር ስጦታ ተደርጓላቸዋል።

በአጠቃላይ በማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን ስር ከ4ሺህ በላይ ተማሪዎች የደብተር ድጋፉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ነው ያሉት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ።

ድጋፉን ያገኙ ተማሪዎች ተግተው በማጥናት ውጤታማ እዲሆኑም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በአበበ የሸዋልዑል

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.