Fana: At a Speed of Life!

ኢንስቲትዩት ከ3 ሚሊየን በላይ ማጣቀሻ መፅሐፍትን በኦንላይን አደራጅቷል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ከ3 ሚሊየን በላይ ማጣቀሻ መፅሐፍትን በኦንላይን ማደራጀቱን አስታወቀ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢነጂነር አብርሃም በላይ እና የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች የኢንስቲትዩቱን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

ኢንስቲትዩቱ የተሽከርካሪ የአስተዳደር ስርዓት፣ የተቋማት የኢሜል መጠቀሚያ፣ የሰራተኞች መታወቂያና ባጅ አስተዳደር ሰርዓት፣ የተቀናጀ የትራንስፖርት አስተዳደር ስርዓት፣ የከፍተኛ ትምህርት አስተዳደር ስርዓት እና ሌሎች ስርዓቶችንና መተግበሪያዎችን መዘርጋቱንና ማበልፀጉን አስታውቋል።

ከዚህ ባለፈም 3 ሚሊየን 37 ሺህ 443 ማጣቀሻዎችን (የባለቤትነት መብት የተሰጣቸው መረጃዎች፣ የህግ ጉዳዮች፣ የከፍተኛ ትምህርት እና ሌሎች መረጃዎችን ያካተተ) በኦንላይን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ነው የገለጸው።

በተጨማሪም የብሄራዊ የኢኖቬሽን መረጃም ተጠንቶ መጠናቀቁን እና በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳንዱካን ደበበ መናገራቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.