Fana: At a Speed of Life!

ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ተጠባቂውን ጨዋታ ለመምራት ደቡብ አፍሪካ ገቡ

አዲስ አበባ፣ሚያዝያ 14፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተስማ ተጠባቂውን የማማሎዲ ሰንዳውስን እና ፔትሮ አትሌቲኮ ጨዋታ ለመዳኘት ደቡብ አፍሪካ ገብተዋል፡፡
የ2021/22 የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ወደ ፍፃሜው እየተጠጋ ሲሆን በሳምንቱ መጨረሻ አራት ውስጥ የሚገቡ ክለቦች የሚለዩበት የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
ከነዚህ ጨዋታዎች አንዱ የሆነውን የማማሎዲ ሰንዳውስን እና ፔትሮ አትሌቲኮን ጨዋታ ኢትዮጵያዊው ኢንተርናሽናል አርቢተር ባምላክ ተሰማ በዋና ዳኝነት ይመሩታል፡፡
ኢንተርናሽናል ዳኛው ቀደም ሲል በፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ክስ ቀርቦበት በብሄራዊ ዳኞች ኮሚቴ የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ከሚደረግበት አዳማ ከተማ እንዲሰናበቱ መደረጋቸው ይታወሳል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.