Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የነበሩት ኢንጂነር ሰናይት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

ኢንጂነር ሰናይት በኢትዮጵያ ማዕድን ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ከማገልገላቸው በፊት በተለያዩ የመንግስት የስራ ሃላፊነት ውስጥ ሆነው ሲያገለግሉ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

ህልፈታቸውን ተከትሎም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ሃዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

የቀድሞ የስራ ባልደረባችን በነበሩት ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠው ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት እጅጉን አዝኛለሁ ብለዋል፡፡

ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለስራ ባልደረቦቻቸው በራሳቸውና በከተማ አስተዳደሩ ስም መፅናናትን መመኘታቸውን በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.