Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ጀፍሪ ፊልትማን ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ በኩል የታላቁ የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪዎች ተገኝተዋል፡፡
ለልዩ መልዕክተኛው በግድቡ ግንባታና የሶስትዮሽ ድርድር ዙሪያ በሚኒስትሩ ገለጻ ተደርጎላቸዋል።
ጄፍሪ ፊልትማን ከኢትዮጵያ በፊት በግብጽ፣ በሱዳን እና ኤርትራ ጉብኝት ያደረጉ ሲሆን በጉብኝታቸው ከሃገራቱ መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ ትብብርና ቀጠናዊ ጉዳዮች መምከራቸው የሚታወስ ነው።
ልዩ መልእክተኛው እስከ ግንቦት 5 ቀን 2013 ዓ.ም በአፍሪካ ሃገራት ከሚኖራቸው ቆይታ በተጨማሪ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅትና የአፍሪካ ህብረት የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ከፖለቲካ አመራሮችና ከሰብአዊ እርዳታ ተቋማት ሃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የልዩ መልዕክተኛው ጉብኝት አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ በሚገኙ ሃገራት ያሉ የፖለቲካ፣ የጸጥታና ሰብአዊ ችግሮች በዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንዲፈቱ ያላትን ቁርጠኝነት ማረጋገጥና በቀጠናው ያላትን የፖሊሲ ትብብር የማጠናከር አላማ ያለው ነው።
ጄፍሪ ፊልትማን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

በፍሬህይወት ሰፊው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.