Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በከተማዋ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለመደገፍ ከባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል።

ውይይቱ ባለሃብቶቹ ሊያደርጓቸው በሚገቡ ድጋፎች ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን፥ ባለሃብቶቹ የኮሮና ቫይረስ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት እንደ ሃገር ለመመከት አቅማቸው በፈቀደው ሁሉ የከተማ አስተዳደሩ እየሰራ ያለውን የመከላከል ስራ እንደሚደግፉ ተናግረዋል።

ኢንጂር ታከለ ኡማ ባለሃብቶቹ በራሳቸው ተነሳሽነት ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም ወረርሽኙን ለመግታት ላሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ለሚሰራቸው ስራዎች አድናቆት እንዳላቸው የጠቆሙት ባለሃብቶቹ በቀጣይነትም ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በቅርበት ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው መናገራቸውን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.