Fana: At a Speed of Life!

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 11 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የማዕድን እና ኢነርጂ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዑስማን ዲዮን ጋር ተወያይተዋል።

ኢንጂነር ታከለ በማዕድን ዘርፉ እየተከናወነ ካለው የፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያና ሪፈሮርም ጋር በተያያዘ ገለጻ አድርገዋል፡፡

የማዕድን ዘርፉ ኢንቨስትመንት እንዲያድግ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተም ውይይት ተደርጓል፡፡

የዓለም ባንክ በማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች በተለያዩ መንገዶች ድጋፍ እንደሚያደርግም ኃላፊዎቹ ገልጸዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለማዕድን ዘርፉ የህግ ማዕቀፍ ዝግጅት ሙያዊ እና የአቅም ግንባታና ኢንቨስትመንት ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

በተጨማሪም በቴክኖሎጂ የተደገፈ የሀብት ክምችት ፍለጋ በተለይም በዲጂታላይዜሽን ዙሪያ አብረው ለመስራት መስማማታቸውን ኢንጂነር ታከለ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.