Fana: At a Speed of Life!

ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ማጠናከር አላማው ያደረገ የኢትዮ ቻይና ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ቻይና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ማጠናከርን አላማው ያደረገ ምክክር በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ አካሄዱ፡፡

ምክክሩ በገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዢያን እንዲሁም ሌሎች የስራ ሃላፊዎች በተገኙበት መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ቻይና ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ ያደነቁት ሚኒስትሩ፥ የቻይና መንግስት ከመስሪያ ቤታቸው ጋር በተለያዩ ዘርፎች በትብብር እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተለይም በሃገሪቱ የኢኮኖሚ ሪፎርም ፕሮግራም፣ በመሰረተ ልማት እና የሰው ሃይል ልማት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አያይዘውም በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለው የኢኮኖሚ ትብብር ከጊዜ ወደጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱን ጠቁመው፥ ኢትዮጵያ ሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያን በመከተል ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባት እንደማለሟም ከቻይና ኢኮኖሚያዊ እድገት ትምህርት እንደምትወስድም አንስተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዛሆ ዢያን በበኩላቸው፥ ሃገራቸው ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ ቁርጠኛ መሆኗን አስረድተዋል፡፡

አያይዘውም የሃገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና የሚያረጋግጡ ነባር እንዲሁም አዲስ ኢኮኖሚያዊና የአቅም ግንባታ ፕሮጀክቶችን ማፋጠን ያለውን ጠቀሜታ በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.