Fana: At a Speed of Life!

ኢዜማን ጨምሮ 5 ፓርቲዎች የምርጫ ምልክቶቻቸውን ቀይረው እንዲያቀርቡ ቦርዱ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ እየተከናወነ እንደሆነ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት እስከአሁን ድረስ 45 ያህል ፓርቲዎች ምልክቶቻቸውን ያስገቡ ሲሆን አምስት ፓርቲዎች የመረጧቸው ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ ጥሪ ተደርጎላቸዋል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ( ኢዜማ)  የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ፤

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ  የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ፤

የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ፤

የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ – ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በሆኑ፤

የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያቂ ንቅናቄ- ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በመሆኑ  የምርጫ ምልክቶቻቸውን  ቀይረው እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።

በተጨማሪ  የኦሮሞ ነጻነት ግንባር -ህጋዊ ሃላፊነት በተሰጠው አካል ምልክታቸውን እንዲመርጡ ተጠይቆ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የምርጫ ምልክት አስገብተዋል ብሏል የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ።

በዚህ መሰረት የምርጫ ምልክቶቻቸውን ያላስገቡ፣ እንዲቀይሩ የተገለፀላቸው ወይም መቀየር የሚፈልጉ እስከ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንዲያጠናቅቁ ቦርዱ እያሳስቧል።

የጸደቁ ምልክቶችን እና የፓርቲዎችን ዝርዝር ሂደቱ ሲጠናቀቅ ይፋ እንደሚያደርግ ቦርዱ አስታውቋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.