Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ በሞቃዲሾ እየታየ ያለው ያለመረጋጋት እንዳሳሰበው ገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በሞቃዲሾ እየታየ ያለው ያለመረጋጋት እንደሚያሳስበው ገለፀ፡፡
 
ኢጋድ በሶማሊያ የፖለቲካ መረጋጋት እንዳይፈጠር የሚደረገው ወከባ ተገቢነት የሌለው ነው ሲል ኮንኗል፡፡
 
እየታየ ያለው ያለመረጋጋት ሀገሪቷን ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ላይ ጥላ ሊያጠላ እንደሚችልም አሳስቧል፡፡
 
በሀገር ግንባታ፣ ሀገሪቷ በምታካሂደው ምርጫ እና ሽብርተኞችን መዋጋት ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችልም ነው ኢጋድ የገለፀው፡፡
 
ፖለቲከኞችም ነገሮችን ከማባባስ የሶማሊያን ህዝብ ያማከለ ሰላማዊ፣ ነፃ እና ተአማኒነት ያለው ያልተጓተተ ምርጫ ለማካሄድ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.