Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ እና ጣሊያን በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ከጣሊያን ጋር በቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ተስማሙ።

የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ከጣሊያኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሉዊጂ ዲ ማዮ ጋር ተወያይተዋል።

ዶክተር ወርቅነህ በዚህ ወቅት ጣሊያን የኢጋድ የረጅም ጊዜ ወዳጅና የኢጋድ አጋሮች ፎረም ሊቀ መንበር መሆኗን አስታውሰዋል።

በውይይታቸው ወቅትም ኢጋድና ጣሊያን በድርቅ፣ ቀጠናዊ የሰላም ሂደትን ለመደገፍ እና ህገ ወጥ ስደትን ለመከላከል በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል ብለዋል።

ከዚህ ባለፈም ለኢጋድ የእንስሳት ህክምና ትምህርት ቤት ድጋፍ ማድረግ በሚቻልበት አግባብ ላይ መስማማታቸውንም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.