Fana: At a Speed of Life!

ኢጋድ 2ኛውን ዓለም ዓቀፍ ሳይንሳዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) 2ኛውን ዓለም ዓቀፍ ሳይንሳዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።

‘በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት የሰዎች እንቅስቃሴ’ በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው ዓለም ዓቀፍ ሳይንሳዊ ጉባኤ ትኩረት በስደተኞችና በተፈናቃዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየው በጉባኤው መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት፤ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በቀጣናው ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና አሳድሯል።

በተለይም ስደተኞችና ተፈናቃዮች ለከፋ ጉዳት ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ የስደተኞችና የተፈናቃዮችን ተጋላጭ ጨምሮ እንደነበር አንስተዋል።

የኢጋድ አባል አገራትና ተቋሙ የኮቪድ-19 ጫናን ለመቀነስ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን ያስታወሱት ዋና ጸሐፊው፤ ምርመራ በማድረግና የኢኮኖሚ ድጋፍ በማድረግ የወረርሽኙን ጫና ለመቀነስ እየተሰራ እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የኢጋድ ሳይንሳዊ ጉባኤ ለሶስት ቀናት የሚካሄድ ሲሆን 28 ጥናታዊ ጽሁፎች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.