Fana: At a Speed of Life!

ኤለን መስክ ካርበንን ማከማቸት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ላቀረበ 100 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ደቡብ አፍሪካ አሜሪካዊው ቢሊየነር ኤለን መስክ ካርበንን በማከማቸት ወይም በመያዝ የከባቢ አየር ጉዳትን መቀነስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ላቀረበ 100 ሚሊየን ዶላር ሽልማት አዘጋጀ።

የስፔስ ኤክስ እና በፀሀይ ሀይል የሚሰሩ ተሽከርካሪዎች አምራች ኩባንያ የሆነው የቴስላ መስራች ኤለን መስክ በዓለም በ185 ቢሊየን ዶላር ቀዳሚው ባለፀጋ ነው።

ኤለን መስክ በትዊተር ገፁ ላይ ካርበንን መያዝ የሚያስችል ምርጥ ቴክኖሎጂ ላቀረበ 100 ሚሊየን ዶላር አበረክታለሁ ብሏል።

ካርበንን ማከማቸት ማለት ከምንጩ ካርበንን በመያዝ እና በማከማቸት ከውሰጡ ያለውን ከባቢ አየር የሚጎዳ ጋዝ ማስወገድ እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ።

በዓለም ላይ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ግለሰቦች ከዚህ በፊት የካርበን መያዣ ቴክኖሎጂ ለመስራት ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.