Fana: At a Speed of Life!

ኤምባሲው የሳዑዲን የመኖሪያ ፈቃድ ህግን ተላልፈው የተገኙ ስምንት ታዳጊ እና ሁለት ታማሚ ዜጎችን እንዲፈቱ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የመኖሪያና ሥራ ፈቃድ ህግን ተላልፈው የተገኙ ስምንት ታዳጊ ወጣት ዜጎችን ከእስር ማስፈታቱን አስታወቀ።

ኤምባሲው ሪያድ ከተማ በህግ አስከባሪ ተይዘው የነበሩ ዜጎችን ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር በመነጋገርና ሃላፊነት በመውሰድ እንዲፈቱ ማድረጉን አስታውቋል።

በተጨማሪም በተለያዩ ጊዜያት የታመሙ ዜጎች ከተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች እንዲፈቱ በማድረግና በሃላፊነት በመቀበል ዘመዶቻቸው ጋር እንዲሆኑና የህክምና ክትትል እንዲያገኙ ሲያደርግ መቆየቱንም አስታውሷል።

በተመሳሳይ በህመም ላይ የነበሩ ሁለት ዜጎች ተገቢውን ህክምና እንዲያገኙ ከነበሩበት ፖሊስ ጣቢያ እንዲፈቱ አድርጓል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.