Fana: At a Speed of Life!

ኤርትራውያንን ጨምሮ የሌሎች አገራት ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ፍላጎት አላቸው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በውጭ አገራት የሚኖሩ ኤርትራውያንን ጨምሮ የሌሎች አገራት ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ፍላጎት ማሳየታቸውን በእንግሊዝና በአሜሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመላው ዓለም ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች አንድ ሚሊየን ዳያስፖራዎች ወደ አገር ቤት እንዲመጡ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የዳያስፖራው ማህበረሰብ አባላት ሌሎች የውጭ አገር ዜጋ ጓደኞቻቸውንና ወዳጆቻውን ወደ ኢትዮጵያ እንዲሄዱ ቅስቀሳ እየተደረገ መሆኑን ኢዜአ ያነጋገራቸው በማንችስተር እና በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ የሚኖሩ ኢትዮያውያን ገልጸዋል፡፡
ለኢትዮጵያ ወዳጆች “ባክ ቱ ዘ ኦሪጅን” ወይም “ወደ ቀደምት የሰው ዘር መገኛ ይምጡ” በሚል እሳቤ ወደ ምድረ ቀደምት አገር ኢትዮጵያ እንዲመጡ ጥሪ እየተደረገ መሆኑንም አመልክቷል።
እየተደረጉ ባሉ ቅስቀሳዎች በርካታ የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ፍላጎት ማሳየታቸውንና ይሄም ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስተያየት ሰጭዎቹ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪ በእንግሊዝ ለሚገኙ የኢትዮጵያ ወዳጆች በኢትዮጵያ ያለውን እውነታ የማስረዳት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት፡፡
ከኢትዮጵያውያንና ከትውልደ ኢትዮጵያውያን በተጨማሪ ኤርትራውያን እና ሌሎች የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ አገር ቤት እንደሚመጡም ጠቁመዋል።
በአሜሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ የማሳወቁ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቅሰው÷ በዚህም በርካቶች ጥሪውን ተቀብለው ወደ አገር ቤት ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ዳያስፖራዎች ቢያንስ አንድ የውጭ አገር ዜጋ ወደ ኢትዮጵያ ይዘው እንዲመጡ ጥሪ ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.