Fana: At a Speed of Life!

“ኤች አር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ተካሄደ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ኤችአር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ተካሂዷል።

ኋይት ሃውስ ፊት ለፊት በተካሄደው ሰልፍ “ማዕቀብ ይገድላል”፣ “ጸረ-ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና አሜሪካ የሆኑትን ረቂቅ ሕጎች እንቃወማለን”፣ “ኤችአር 6600” እና ኤስ 3199 ይሰረዙ” እና  “ፍላጎትን በኃይል ለመጫን የሚደረግን ማንኛውም ድርጊት እንቃወማለን፤ አንቀበልም” የሚሉ መልዕክቶች መተላለፋቸውን ኢዜአ ሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበር የዋሺንግተን ግብረ ኃይልን ጠቅሶ ዘግቧል።

ረቂቅ ሕጎቹ ኢትዮጵያን እንዲሁም የኢትዮጵያና አሜሪካን የረጅም ጊዜ ግንኙነት የሚጎዱ በመሆናቸው በፍጥነት መሰረዝ አለባቸው የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ላይ ተሰምተዋል።

ሕጎቹ በኢትዮጵያ ሰላምን ለማምጣት እየተደረገ ያለውን ጥረት እውቅና ያልሰጠና የሰላም ሂደቱን አሉታዊ ተጽእኖ የሚያሳድር ነው ብለዋል ሰልፈኞቹ።

“ኤችአር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን በመቃወም በኋይት ሃውስ ፊት ለፊት የሚካሄደው ሰልፍ በቋሚነት በየሳምንቱ እንደሚከናወን የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማህበር የዋሺንግተን ግብረ ኃይል አስታውቋል።

በተያዘዘ ዜና “ኤችአር 6600” እና “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ ከነገ በስቲያ በኒው ጀርሲ ግዛት ይካሄዳል።

ሰልፉ የ “ኤስ 3199” ረቂቅ ሕግ አርቃቂ ሴናተር ሮበርት ሜኔንዴዝ (ኒው ጀርሲ) ቢሮ ፊት ለፊት እንደሚካሄድ ከኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ተስፋ ለኢትዮጵያ ድርጅት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.