Fana: At a Speed of Life!

ኤኮን የ #በቃ ንቅናቄን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ- አሜሪካዊው የሙዚቃ አቀንቃኝ ኤኮን የ #በቃ ንቅናቄን ተቀላቅሏል፡፡

በዓለም የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ ተጽዕኖ ፈጣሪ አርቲስቶች እና የተለያዩ ባለሙያዎች ንቅናቄውን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ዝነኛው ሙዚቀኛ ኤኮን ኢትዮጵያውያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ፣ አፍሪካውያን ፣ እና የኢትዮጵያ ወዳጆችን ጨምሮ ዓለምን እያነቃነቀ ያለውን የ #በቃ ን ንቅናቄ በመደገፍ ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ አለፍ ሲልም በአፍሪካ ላይ የሚያደርጉትን ያልተገባ ጫና ተቃውሟል፡፡

አርቲስቱ በኢንስታግራም ገጹ ባሰፈረው መልዕክት ነው ንቅናቄውን መቀላቀሉን ያስታወቀው፡፡

ኤኮን ድምጻዊ፣ የሙዚቃ ፕሮዲውሰር እና ስራ ፈጣሪ አርቲስት ሲሆን፥ ለግራሚ አዋርድ ሶስት ጊዜ ታጭቷል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.