Fana: At a Speed of Life!

ኤይር ባስ በ2035 ከብክለት ነጻ የሆነ አውሮፕላን ይፋ እንደሚያደርግ ማቀዱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)  ኤይር ባስ በ2035 ከብክለት ነጻ በሆነ አውሮፕላን አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን አስታወቀ፡፡

ኤይር ባስ ላቀደው ከብክለት ነጻ ለሆነ አውሮፕላኑ ሃይድሮጅንን በኃይል ምንጭነት ይጠቀማል ነው የተባለው፡፡

የኩባንያው ኃላፊ በግል አቬይሽ ዘርፍ እርምጃው ታሪካዊ መሆኑን ጠቅሰው በኢንዱስትሪ ሽግግር የመሪነት ሚናን መጫወት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አየር መንገዶችና አውሮፕላን አምራቾች  የካርበን ልቀትን እንዲቀንሱ ግፊት በርትቶባቸዋል፡፡

ኃላፊው አሁን ይፋ የሆነው ዕቅድ በዘርፉ አየርንብረትን መሰረት አድርገው የሚነሱ ግፊቶችን እንደሚቀንስ ገልጸዋል፡፡

በዕቅዱ የተካተቱት ሦስት ዓይነት አውሮፕላኖች ሲሆኑ በሃይል አጠቃቀም፣ በሚያጓጉዙት የሰው ብዛትና በሚሸፍኑት ርቀት ይለያያሉ ተብሏል፡፡

በመጨረሻም ዘርፉ በሚያደርገው ሽግግር ለምርምርና ለቴክኖሎጂ የመንግስታት ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ተገልጿል፡፡

 

ምንጭ፡- ሲኤንኤን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.