Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው ለተፈናቀሉ ወገኖች የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ /ኢመደኤ/ በአሸባሪዉ የትህነግ ቡድን ከቤት ንብረታቸዉ ለተፈናቀሉ የአፋር ክልል ነዋሪዎች የ5 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛዉ እንደገለጹት÷ ድጋፉ በተቋሙ አመራርና አባላት ስም የተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ድጋፉም÷ ኤጀንሲዉ ከሚያደርገዉ ቴክኒካል ድጋፍ በተጨማሪ፤ በአሸባሪዉ የትህነግ ቡድን በአፋር ክልል ለወደሙ መሰረተ ልማቶች እና ከቀያቸዉ ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች የሚውል ነው ተብሏል፡፡
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አወል አርባ በበኩላቸዉ÷ በወራሪዎች ግፍ የተነሳ ስቃይ እና እንግልት እየደረሰበት ለሚገኘው ህዝባቸው ኤጀንሲዉ ድጋፍ በማድረጉ ምስጋና አቅርበዋል።
በአሁኑ ሰዓት 200 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በአፋር ክልል ብቻ ከቀያቸው መፈናቀላቸዉን ገልጸው÷ የተደረገው ድጋፍ ተፈናቃዮቹን ወደነበሩበት አኗኗር ለመመለስ ያግዛል ብለዋል፡፡
ወደፊትም ከኢጀንሲዉ ጋር በቴክኖሎጂ ሽግግር በጋራ እንሰራለን ሲሉም አክለዋል ርዕሰ መስተዳድሩ።
የኤጀንሲዉ አባል ሆነዉ የመዝመት ጥያቄ ላቀረቡ አባላትም አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ መላካቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.