Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው ከ6 ሜትር ርቀት በሁለት ቋንቋ መረጃን የሚሰጥ ከንክኪ ነጻ የሆነ የእጅ ማጽጃ ማሳሪያ ጥቅም ላይ አዋለ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢንፎሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ከ6 ሜትር ርቀት በሁለት ቋንቋ መረጃን የሚሰጥ ከንክኪ ነጻ የሆነ የእጅ ማጽጃ ማሳሪያ ጥቅም ላይ አዋለ።

የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የሚረዳ መረጃን የሚሰጥና ከንክኪ ነጻ የሆነ የእጅ ማጽጃ ማሳሪያ ጥቅም ላይ አዉሏል።

ይህ መሳሪያ በዋነኝነት የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘር እና አልኮል ያለ እጅ ንክኪ መጠቀም ከማስቻሉም በላይ ከ6 ሜትር ርቀት ውስጥ ሰዎች በአካባቢው ላይ ሲገኙ በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ ቋንቋ የእጅ ማጽጃውን እንዲጠቀሙ መረጃን በመስጠት ለማንቃት ይረዳል።

ኤጀንሲዉ የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ጀምሮ ቫይረሱን ለመካላከል ሃገሪቱ በምታደርገዉ እንቅስቃሴ አጋዥ የሆኑ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ላይ እየተሳተፈ ሲሆን ዛሬ የተዋወቀዉ ዘመናዊ የእጅ ማጽጃ መሳሪያ አንዱ ነዉ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.