Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 30 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት በፌደራል ህብረት ስራ ማህበራት በኩል  እየተሰራ መሆኑን የፌዴራል ህብረት ስራ ኤጀነሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኡስማን ሱሩር ገለጹ።

ዋና ዳይሬክተሩ ከፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ ÷ ከአምራቹ እስከ ሸማቹ በሚደርስ ሰንሰለት ውስጥ ምንም እሴት የማይጨምሩ አካላት ጣልቃ መግባታቸው ለዋጋ ንረት መንስኤ መሆኑን ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ  ቶሎ የሚበላሹ የግብርና ምርቶች ማቆየት የሚያስችል ሁኔታ አለመመቻቸት  ትልቅ ተግዳሮት ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት የሚስተዋለውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት ሚስማርና ቆርቆሮን ጨምሮ የሰብል ምርቶችን  በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚ በማቅረብ ረገድ እየሰሩ የሚገኙ ማህበራቶች መኖራቸውን ገልጸዋል።

የፌዴራል መንግስት የኮሮና ወረርሽኝን ተከትሎ የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር 800 ሚሊየን ብር መመደቡን አቶ ኡስማን  አስታውሰዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም 500 ሚሊየን ብር በአነስተኛ ብድር አቅርቦ በማሀበራቱ በኩል የምርት አቅርቦት ስራ እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ከፌዴራል ህብረት ስራ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ 32 ሚሊየን አባላት ያሏቸው 94 ሺህ የህብረት ስራ ማህበራት ይገኛሉ።

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.