Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በምስራቅ ኢየሩሳሌም ለማካሄድ ያሰበችው የሰፈራ ፕሮግራም ተቃውሞ ገጠመው

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 8 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት እና የአውሮፓ ህብረት እስራኤል በምስራቃዊ ኢየሩሳሌም ዳርቻ ላይ ለማካሄድ ያሰበችውን የሰፈራ ፕሮግራም አወገዙ፡፡

እስራኤል በምስራቃዊ ኢየሩሳሌም ለአይሁድ ሰፋሪዎች 1 ሺህ 250 ቤቶችን ለመገንባት እቅድ እንዳላት መግለጿ ይታወሳል፡፡

የሰፈራ ፕሮግራሙ በጊቫት ሀማቶስ አካባቢ የሚገነባ ሲሆን የግንባታ  ጨረታም ማውጣቷ ተገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት ልዑክ እቅዱ የወደፊቷን ፍልስጤም የሚጎዳ ነው ሲልም አስጠንቅቋል።

በፕሬዚዳንት ትራምፕ ዘመን አሜሪካ የሰፈራ ፕሮግራምን የፈቀደች ቢሆንም አዲስ የተመረጡት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ግን ይህን አካሄድ ይቀይራሉ ተብሎ ይጠበቃል ነው የተባለው፡፡

ዕቅዱን በመቃወም ሰኞ ዕለት አካባቢውን የጎበኙት የአውሮፓ ዲፕሎማቶች በእስራኤል ብሄርተኞች ዘንድ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡

የሰፈራ ፕሮግራሙን የሚቃወሙት ደግሞ ተመራጩ ፕሬዚዳንት ባይደደን ስልጣናቸውን ከመረከባቸው በፊት የእስራኤል ባለሥልጣናት ፕሮጀክቱን በፍጥነት ተግባራዊ ያደርጉታል የሚል አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

እስራኤል በፈረንጆቹ 1967 በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ዌስት ባንክ እና ምስራቅ ኢየሩሳሌምን ከያዘች ጀምሮ 140 ሺህ ቤቶችን በሰፈራ መኘልክ ገንብታለች፡፡

በእነዚህ ጊዜያትም 600 ሺህ አይሁዳውያን በሰፈራው ተጠቃሚ ሆነዋልም ነው የተባለው፡፡

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በበኩሉ የእስራኤልን የሰፈራ ፕሮግራም ህገ ወጥ ናቸው በሚል እውቅና አይሰጣቸውም፡፡

 

ምንጭ፦ ቢቢሲ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.