Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትብብር በሁሉም ዘርፍ ማሳደግ ትሻለች – የእስራኤል የክልላዊና አካባቢ ትብብር ሚኒስትር

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ረታ ዓለሙ ከእስራኤል የክልላዊና አካባቢ ትብብር ሚኒስትር ኦፊር አኩኒስ ጋር ተወያዩ።

ውይይታቸው የሃገራቱን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ አምባሳደር ረታ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በተለይም በምስራቅ አፍሪካ የክልላዊ እና አህጉራዊ ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማጠናከር ስለምታከናውናቸው ተግባራት ገለፃ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ በትብብርና በመከባበር መንፈስ አጋርነትን ለማሳደግ የተጫወተችውን ገንቢ ሚናን በተመለከተም አስረድተዋል።

የእስራኤል መንግሥት የክልላዊና አካባቢ ትብብር ሚኒስትር ኦፊር አኩኒስ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለሁለትዮሽ እና ለቀጠናዊ የኢኮኖሚ ትብብር ትልቅ እምቅ አቅም እንዳላት መገንዘባቸውን ተናግረዋል።

አያይዘውም የእስራኤል መንግሥት ትብብሩን በሁሉም ዘርፍ ለማሳደግ ያለውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅት በኢትዮጵያና በእስራኤል መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

የሁለትዮሽና የቀጠናዊ ኢኮኖሚያዊ ትብብርን ለማጎልበት በጋራ ለመስራት መስማማታቸውንም በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.