Fana: At a Speed of Life!

እነ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ በ8 ተጠርጣሪዎች ላይ ለነሃሴ 22 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 20 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) እነ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ስምንት ተጠርጣሪዎች ቀሪ የዐቃቤ ህግ የቅድመ ምርመራ ምስክር ለመስማት የተቀጠረ ቢሆንም ከ4ኛ እስከ 9ኛ ያሉ ተጠርጣሪዎች የኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ውጤት ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዪት ስላልመጣ ለነሃሴ 22 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ።

በችሎቱ የተገኙት አቶ ጃዋር መሀመድ ውጭ ሀገር ከሚገኙት ልጃቸው እና ባለቤታቸው ጋር በቪዲዮ ኮንፈረንስ አንድ ጊዜ ብቻ መገናኘታቸውን በመግለፅ በድጋሚ እንዲገናኙ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም በዚህ እና በተነሱ ሌሎች አቤቱታዎች ላይ በቀጣይ ቀጠሮ ትዕዛዝ እሰጥበታለሁ ብሏል።
በታሪክ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.