Fana: At a Speed of Life!

እናት ባንክ ከሁለት ተቋማት ጋር በስትራቴጂካዊ አጋርነትና በትብብር አብሮ ለመስራት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) እናት ባንክ ከኢዚቲ የመረጃ ማዕከልና ከሜርሲ ኮርፕስ ጋር በስትራቴጂካዊ አጋርነትና በትብብር አብሮ ለመስራት ተፈራርሟል፡፡

ባንኩ ከሁለቱ ተቋማት ጋር በመተባበር በተለይም ከአረብ አገር የተመለሱ ሴቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን፥ 300 ለሚሆኑ ሴቶች ዋስትና ያለው የስራ እድል እንደሚፈጥር ተገልጿል።

ከተቋማቱ ጋር በመተባበር እድል ላላገኙ እናቶች እና ሴቶች የሚሆን የስራ እድል መፍጠሩን ባንኩ አስታውቋል።

ባንኩ ሲመሰረት አላማ አድርጎ የተነሳው ሴቶችን በኢኮኖሚ ተጠቃሚ ለማድረግ አልሞ መነሳቱን የገለፁት የእናት ባንክ የኮርፖሬት ዘርፍ ምክትል ዳይሬክተሯ ወይዘሮ ገነት ሀጎስ÷ ስራ ለመጀመር ገንዘብ ላጠራቸውና ዋስትና ማቅረብ ለማይችሉ ሴቶችና እናቶች እስከ 300 ሺህ ብር በማበደር ስራ እንዲጀምሩ እየሰራን ነው ብለዋል።

በተጨማሪም በዚህ ፕሮጀክት አማካኝነት በሀገር ውስጥ የስራ እድል በመፍጠር ወደ አረብ ሀገር ሄዶ የመስራትን አመለካከት ለመቀየር ያስችላል ተብሏል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.