Fana: At a Speed of Life!

እናቶች  በኮሮና ቫይረስ ቢያዙም ልጆቻቸውን ጡት ማጥባት  አለባቸው-የዓለም የጤና ድርጅት

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 28 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አዲስ የተወለዱ ሕፃናትን ወይም ልጆችን ጡት ማጥባት የሚሰጠው ጥቅም  የኮቪድ 19 በሽታ ከሚያመጣው ስጋት እጅግ የላቀ  በመሆኑ እናቶች  በኮሮና ቫይረስ ቢያዙም ልጆቻቸውን ጡት ማጥባት አለባቸው ሲል  ዓለም  አቀፉ የጤና ድርጅት ገልጿል።

የዓለም  አቀፉ የጤና ድርጅት ኃላፊ ዶክተር ቴድሮስ  አድሃኖም ÷ምንም እንኳን እናቶች በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ቢያዙም ልጆቻቸውን  ጡት ማጥባታቸው ለህጻናቱ  የሚሰጠው ጥቅም በሽታው ከሚያስከትለው ጉዳት ከፍ ያለ  መሆኑን ተናግረዋል።

ሃላፊው ይህንን የተናገሩት በዓለም  አቀፍ ደረጃ የጡት ማጥባት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት በተከበረበት ወቅት ሲሆን ÷ በኮቪድ- 19 በሽታ የተጠረጠሩ ወይም መያዛቸው የተረጋገጠ  እናቶች እንደሌሎች እናቶች ሁሉ   ህጻናት ልጆቻቸውን ጡት ማጥባት እንዲቀጥሉ መበረታታት አለባቸውም  ብለዋል።

አዲስ ለተወለዱ ሕፃናት እና ልጆች ጡት ማጥባት የሚሰጠው ጥቅም  በኮቪድ-19 ኢንፌክሽኖች ከሚመጣው ስጋት እጅግ የላቀ ነውም ነው ያሉት።

ምንጭ፡-ሮይተርስ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.