Fana: At a Speed of Life!

እንቁላል ከውጭ ሀገር ለማስገባት የተደረገ ስምምነት የለም – ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብርና ሚኒስቴር እንቁላል ከውጭ ሀገር ለማስገባት የተደረገ ስምምነት የለም አለ፡፡

ሰሞኑን በተለያዩ ሚዲያዎች ሚዲያ ከዩክሬን የምግብ ደህንነት እና ሸማቾች ጥበቃ አገልግሎት አገኘነው ባሉት መረጃ ኢትዮጵያ ከዩክሬን እንቁላል ለማስገባት መስማማቷን እና የዩክሬን እንቁላል አምራቾች እንቁላል ወደ ኢትዮጵያ ለማስገባት ፍቃድ ማግኘታቸውን መዘገባቸው ይታወሳል፡፡

ከዚህ በመነሳትም የተለያዩ መገናኛ ብዙኀን መረጃውን በመቀባበል ላይ ይገኛሉ፡፡

በግብርና ሚኒስቴርም ሆነ በንግድ ሚኒስቴር በኩል እንቁላል ከዩክሬንም ሆነ ከሌሎች ሃገሮች ለማስገባት የተደረገ ስምምነት ያልተደረሰ መሆኑን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው፡፡

የእንስሳት ሀብት ዘርፉ በተለይ ደግሞ የዶሮ እርባታ ስራ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ በስራ እድል ፈጠራ እና ኢንቨስትመንት በኩል ከፍተኛ ድርሻ እያበረከተ በመሆኑ እስካሁን ያለውን የዘርፉን ምርታማነት ለመጨመር እና ከዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማሳደግ በ10 ዓመቱ መሪ እቅድ ውስጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ወደ ስራ መገባቱን ግብርና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.